12 ሜይ 2024
ፍኖተ ሰላም
የሸማቾች ኅብረት ሥራ ማኅበራት የመንግሥት ሠራተኞችን የዋጋ ንረት ችግር የሚፈቱ ተቋማት ናቸው
በምዕራብ ጎጃም ዞን እየተፈጠረ ያለውን የዋጋ ንረት በተገቢው ለመቆጣጠር እና የገበያ መረጋጋትን ለመፍጠር ኅብረት ሥራ ማኅበራት ያላቸውን ሚና አጠናክረው እንዲሰጡ እየተደረገ ይገኛል።
ዋና አስተዳዳሪው አክለውም፣ በአሁኑ ሰዓት የሚስተዋለውን የገበያ አለመረጋጋትና ሆን ተብሎ በምርቶች ላይ የሚደረግ አላስፈላጊ የዋጋ ጭማሪን ለመከላከል የዞኑ አስተዳደር ቅድሚያ ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል ብለዋል። ይህም የመንግሥት ሠራተኞች ተከታታይ በሆነ መልኩ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ እንዲያገኙ ያስችላቸዋል ተብሏል። በመሆኑም የሚቋቋሙት ማኅበራት አባላትን ሰፊ በሆነ መልኩ የሚያቀፉ፣ አሁን ያለውን የገንዘብ የመግዛት አቅም መዳከም እና ማኅበራቱ የሚያቀርቧቸውን ምርቶች ታሳቢ ያደረገ በቂ ካፒታል የሚኖራቸው ይሆናል።

